New Arrivals/Restock

መመለስና መታደስ (Amharic Edition) (Afrikaans Edition) Kindle Edition

flash sale iconLimited Time Sale
Until the end
22
18
40

$3.59 cheaper than the new price!!

Free shipping for purchases over $99 ( Details )
Free cash-on-delivery fees for purchases over $99
Please note that the sales price and tax displayed may differ between online and in-store. Also, the product may be out of stock in-store.
New  $5.99
quantity

Product details

Management number 219443735 Release Date 2026/05/03 List Price $2.40 Model Number 219443735
Category

አሁን ባለንበት ዘመን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመድረስ ጂ.ፒ.ኤስ (GPS) እንጠቀማለን። ጂ.ፒ.ኤስ ሳተላይትን የሚጠቀም ቴክኖሎጂ ሲሆን፣ ከአንድ መልክዓ ምድር ወደ ሌላ መልክዓ ምድር ለመድረስ ተመራጭና አቋራጭ መንገዶችን እየመራ የሚያደርስ ነው። መንፈሳዊ ሕይወታችንም ወደ መዳረሻው ማምራት ያለበት የጉዞ እንቅስቃሴ ነው። የምንሄድበትን መዳረሻ ካላወቅን፣ ጂ.ፒ.ኤስ ልንጠቀም አንችልም። ጂ.ፒ.ኤስ ጥቅም የሚሰጠን መዳረሻችንን ካወቅን ነው። መዳረሻችንን ካላወቅን፣ ጂ.ፒ.ኤስ ሊመራን አይችልም። ስለዚህ፣ ጂ.ፒ.ኤስ ስንጠቀም ሦስት ቦታዎች አሉ፦ ያለንበት፣ የምናልፍበትና የምንደርስበት።ይህ መጽሐፍ በእነዚህ ሦስት ጽንሰ ሐሳቦች ላይ የተገነባ ነው፦ ያለንበት፣ የምናልፍበትና የምንደርስበት። መንፈሳዊ ሕይወታችን መዳረሻ (destiny) አለው። ነገር ግን ወደዚህ መዳረሻ መድረስ የምንችለው አሁን ያለንበትን ካወቅንና ወደ መዳረሻችን ለመድረስ መከተል ያለብንን መንገድ ስናውቅ ነው። ችግራችን መዳረሻችንን አለማወቅ ብቻ ሳይሆን፣ አሁን ያለንበትን በቅጡ ላንረዳው እንችላለን። እግዚአብሔር በቃሉ ውስጥ ያለንበትንም ሆነ የምንደርስበትን ያሳየናል። ያለንበትንና የምንደርስበትን ማሳየት ብቻ ሳይሆን፣ ካለንበት ተነሥተን ወደ መዳረሻችን የሚወስደንንም መንገድ ያሳየናል። ስለዚህ፣ መንፈሳዊ ጉዞአችን የተሳካ እንዲሆን ያለንበትን፣ የምናልፍበትንና የምንደርስበትን ማወቅ ይገባናል።ከዚህ አንጻር፣ ይህ መጽሐፍ በእነዚህ በሦስት ክፍሎች የተገነባ ነው። የመጀመሪያው ክፍል፣ ያለንበትን በተመለከተ የነፍሳችንን ሁኔታ እንመለከታለን። ያለንበት ሰፈር የነፍሳችንን ባሕሪ የሚያሳይ ነው። ያለንበትን ሰፈር ባሕሪ ማወቃችን ነው ያለንበትን አውቀን ካለንበት እንድንነሣ የሚያደርገን።በመጀመሪያው ክፍል ያለንበትን ሰፈር ባሕሪ ከተመለከትን በኋላ፣ በሁለተኛው ክፍል የምንመለከተው የምናልፍበትን ነው። በዚህ ምድር ላይ በተለያዩ ውጣ ውረዶች እያለፍን ነው የምንኖረው። ነገር ግን የምናልፍበት ወደ መዳረሻችን የሚያደርሰን መሆን አለበት። የምናልፍበት ከመዳረሻችን ጋር ያለውን ግንኙነት ካላየን፣ የምናልፍበት አጋጣሚ እንጂ ብዙ ትርጉም የሚሰጠን ነገር አይሆንም። ስለዚህ፣ በዚህ በሁለተኛው ክፍል የጉዞውን ባሕሪ እንረዳለን። የምናልፍበት አጋጣሚ ሳይሆን፣ ከፍታም ይሁን ዝቅታ ወደ መዳረሻችን እንዲሆን ለማድረግ እንተጋለን። በሦስተኛውና በመጨረሻው ክፍል ደግሞ መዳረሻችንን እንመለከታለን። የመዳረሻችንን ታላቅነት ስናይ፣ ካለንበት ሰፈር ለመነሣትም ሆነ ወደ መዳረሻችን ለመዘርጋት ጉጉትና አቅም እናገኛለን። ስለዚህ፣ ይህ መጽሐፍ ስላለንበት፣ ስለምናልፍበትና ስለምንደርስበት የሚተርክ የጉዞ መጽሐፍ ነው። Read more


Correction of product information

If you notice any omissions or errors in the product information on this page, please use the correction request form below.

Correction Request Form

Product Review

You must be logged in to post a review